የኢትዮጵያ ሳምንት በወዳጅነት ፓርክ ተከፈተ

ግንቦት 10/2013 (ዋልታ) – ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 የሚቆይ የኢትዮጵያ ሳምንት የተባለ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት መርሀ ግብር ዛሬ ተከፍቷል።
በወዳጅነት ፓርክ በተከፈተው በዚህ የኢትዮጵያ ሳምንት ዝግጅት ላይ ሁሉም ክልሎች ባህላቸውንና ማንነታቸወን የሚያሳዩ አውደ ርዕዮችንና ያላቸውን ሀብት ይዘው ይቀርባሉ፤ ያስተዋውቃሉ ተብሏል።
መርሀ ግብሩ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተከፍቷል።
በዚሁ መርሀ ግብር መክፈቻ ላይ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃለፊዎች ተገኝተዋል።