በ10 ወራት ከወጭ ንግድ 2.8 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ግንቦት 11/2013 (ዋልታ) – ባለፉት 10 ወራት ከወጭ ንግድ 3.29 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 2.8 ቢሊየን ዶላር ገቢ እንደተገኘ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገው ገቢ ጋር ሲነፃፀር በ380 ሚሊየን ዶላር ማለትም የ16 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡