መጋቢት 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲን በጊዜያዊነት ማገዱን አስታወቀ፡፡
ቦርዱ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ (ኦነን) ጠቅላላ ጉባኤውን አስመልክቶ የቀረቡ አጠራጣሪ ሰነዶችን አስመልክቶ ምርመራ እንዲደረግ ለፌደራል ፖሊስ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጾ ምርመራው ተጣርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፓርቲው በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 98/3 መሰረት መታገዱን አስታውቋል።
ፓርቲው የታገደው ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቆጠራ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ቦርዱ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡