የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት መኪናዎች ተርሚናል ተመረቀ

 

የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት መኪናዎች ተርሚናል ሲመረቅ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – በፌዴራል መንገዶች ባለስልጣን የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት መኪናዎች ተርሚናል ተመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አወል ዋግሪስ ፣ የጅቡቲ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሙሳ መሃመድ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እንዲሁም ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አወል ዋግሪስ በመክፈቻ ንግግራቸው ለተርሚናሉ መከፈት የጅቡቲ መንግስት ለሰጠው ድጋፍ አመስግነዋል።

ተርሚናሉ በየጊዜው እየጨመረ ለመጣው ወጪ ገቢ ሸቀጦችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም የተርሚናሉ መከፈት የሁለቱ ወንድማማቾች ህዝብ ግንኙነት በኢኮኖሚ ትስስርም እየተጠናከረ መሄዱን እንሚያመላክት ተናግረዋል፡፡
(ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት)