የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ተጀመረ

ሚያዚያ 15/2013 (ዋልታ) – አራተኛው ሃገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዛሬ በአሶሳ ተጀመረ።
በፎረሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

“የምሁራን ተሳትፎ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ” በሚል መሪ ሃሳብ ፎረሙ እስክ ነገ ይቀጥላል።

ዓላማው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ሀገራዊ ጉዳዮችን ማጠናከር እንደሆነ ተገልጿል።

በአሶሳ ዪኒቨርሲቲ በተመጀመረው ፎረም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌስር አፈወርቅ ካሱ እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና ክልል አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።