አምራች እና አገልግሎት ሰጭ ኢንዱስትሪዎች የካይዘን ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ጥራትና ምርታማነታቸውን በቀጣይነት በማሻሻል በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚረዳ ሀገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
ኮንፈረንሱ “ካይዘን ለዘላቂ ተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት እና በኢፌዴሪ ሲቨል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዘጋጀ ነው።
በካይዘን አመራር ፍልስፍና የተካሄዱ የጥናት እና ምርምር ውጤቶችም በኮንፈረንሱ እየቀረቡ ነው።
በምርምር ኮንፈረንሱ የካይዘን አመራር ፍልስፍናን በመተግበር ለውጥ ያስመዘገቡ ተቋማት ተሞክሯቸውን ያቀርባሉ።
ኮንፈረንሱ እንደ ሀገር ተቋማዊ የአመራር አቅም በመገንባት ጥራት እና ምርታማነት በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዝ ነው ተብሏል።
ሀገራዊው የምርምር ኮንፈረንሱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
(በየሻምበል ባምላኩ)