የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ጥር 4/2014 (ዋልታ) የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል ከአገልግሎት ውጭ ሆነው ለነበሩ መሰረተ ልማቶች እና የወደብ ማሽነሪዎች አስፈላጊውን ጥገና በማድረግ፣ የሰው ኃይል፣ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን እንዲሁም አስፈላጊ ግብዓቶችን አሟልቶና እንደገና አደራጅቶ ከሰኞ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በኮምቦልቻ ከተማ ያሉ የኢንዱስትሪ ተቋማት ከደረሰባቸው ጉዳት ተላቀው ወደ ስራ እየተመለሱ ወደቡ ወደ አገልግሎት መመለስ አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች በፍጥነት ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማስቻል ምርታማነታቸውን ለማስቀጠል ወሳኝ ሚና እንዳለው ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህንን ለማድረግም ድርጅቱ ለእነዚህ ተቋማትና ደንበኞች ዕቃቸው በፍጥነት ተጓጉዞ አገር ውስጥ የሚገባበትን ልዩ ሁኔታ ያመቻቸ መሆኑን አስታውቋል፡፡