የኮሪያ ሆስፒታል አራት የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ

ሚያዚያ 20/2014 (ዋልታ) የኮሪያ ሆስፒታል አራት የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደርጓል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ አንዱ አጋፔ ቪዥን ሴንተር የሚሰኝ ሲሆን ባለ ስምንት ወለል ህንፃ ግንባታ ሲሆን፤ ይህም ህንፃ በውስጡ ካርዲዮሎጂ፣ ኒዮሮሎጂ፣ ካስትሮሎጂና የካንሰር ማዕከልን በውስጡ ይይዛል ተብሏል።

የአጋፔ ቪዥን ሴንተር ፕሮጀክት በተለይ እንደ ልብ እና ካንሰር ባሉ ህመሞች ምክንያት ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ዜጎች በሀገር ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ያስችላል።

ሌላው የፕራይሜሪ ብር ሴንተር ሲሆን ይህም ሁለት ፎቆች ሲኖሩት አቅመ ደካሞች በዝቅተኛ ክፍያ አሊያም በነፃ መታከም የሚችሉበት ነው ተብሏል።

የሆስፒታሉ ኮሌጅ ከሚይዛቸው ተማሪዎች በተጨማሪ 50 ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችለውን የማስፋፊያ ፕሮጀክትም ይፋ አድርጓል።

በአዲስ አበባ በ50 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ውስጥ የመንግስት ጤና ተቋማት ባልደረሱባቸው ቦታዎች አራት ክሊኒኮችን እንደሚገነባ ያስታወቀው ኮሪያ ሆስፒታል፤ በቅርቡ የአንዱን ክሊኒክ ግንባታ እንደሚጀምርም አስታውቋል።

በትዕግስት ዘላለም