ኮቪድ-19ን በመከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ጀምሮ ይካሄዳል

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ6 ወራት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የጤና ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይቷል።

በአሁን ወቅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ ይገኛል። ሆኖም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ መጠን ቢጨምርም በመከላከያ መንገዶች አተገባበር ላይ ክፍተት እንዳለ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለ6ወራት የሚቆየው የንቅናቄ ዘመቻ የትግበራ አቅጣጫው እንድናገለግሎ የአፍና አፍንጫ ጭምብል ያድርጉ፣ የተማሪዎች ማህበረሰብ አቀፍ የጤና እንቅስቃሴ፣ እኔም ያገባኛል፣ የጭምብል ባንክ ማሰባሰብ ዋነኞቹ ናቸው።

ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እንደ ችግር የሚነሱ ነጥቦች ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት በትላልቅ መድረኮች አካላዊ ርቀት አለመጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ ጭምብል አለማድረግ፣ መመሪያ 30 ተግባራዊ አለመሆን እንዲሁም ህብረተሰቡ ለወረርሽኙ ያለ ትኩረት መቀነስ ዋነኞቹ መሆናቸው ተገልጿል።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ፣ የጤና ሚኒስቴር ደኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ወረርሽኙን መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በንቅናቄ ዘመቻው ዙሪይ ከምክር ቤት አባላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በኢትዮጵያ 1 ሚለየን 836 ሺህ 527 ሰው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ያደረገ ሲሆን፣ 127 ሺህ 227 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ 1 ሺህ 966 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።

(በሀኒ አበበ)