የኮቪድ-19 ጫናን በመቋቋም በሆስፒታሎች የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

ግንቦት 03/2013 (ዋልታ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጫናን በመቋቋም በሆስፒታሎች የተሰሩ ተግባር ተኮር ስራዎች አበረታች ናቸው ሲሉ የጤና ሚኒስተር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ሪፎርም ማዕቀፍ ውስጥ የተካተቱ ሆሰፒታሎችን በዛሬው እለት የጤና ሚኒስተር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ጫላ እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቷል::
በሀገሪቱ ባሉ ሆስፒታሎች መካከል የልምድ እንዲሁም የእውቀት ሽግግርን እሳቤን የያዘው የሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ውድድሩ የእለቱ የ3ኛ ዙር ተሸላሚ የህክምና ተቋማትም በሶስት የተለያዩ የትኩረት መስኮች መመዘኛ መስፈርት ያለፉ መሆናቸው ተመላክቷል::
የኢትዮዽያ የሆስፒታሎች ጥምረት ሆስፒታሎች እርስ በእርስ የሚማማሩበትን እሳቤ ይፈጥራል ያሉት ዶ/ር ሊያ ታደሰ መሰል ስራዎች የውድድር መንፈስን በማጎናፀፍ ለተሻለ ስራ በር ይከፍታሉ ብለዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ከእውቅናው በዘለለ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ሆስፒታሎች ሽልማት አበርክቷል::
(በሄብሮን ዋልታው)