የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የ”ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን መወሰን

መስከረም 26/ 2014 (ዋልታ) የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የ “ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን ተወሰነ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ለኢትዮጵያ አንድ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስፈልጋት በቀረበው ትንታኔ መነሻነት የቀድሞ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የ “ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን መወሰኑን አስታውቋል።
ተጠሪነቱም ለትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ለፓርላማው ቀርቦ በአዋጅ መደንገጉ ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ልዩ ባህርይን ተላብሶ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።