የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ግዙፍ የኢንቨስትመንት አቅም እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ


ሰኔ 20/2013 (ዋልታ) – የኳታር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ግዙፍ የኢንቨስትመንት አቅም እንዲጠቀሙ በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ጥሪ አቀረቡ።
በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አምባሳደሮች፣ ባለሃብቶች፣ ምሑራንና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የተሳፉበት ምክክር ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መነሻ፣ የቡና መገኛና የሌሎች ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤት መሆኗን አመልክተው፤ ኳታራውያንና የመድረኩ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ድንቅ የተፈጥሮ ስፍራዎችን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።
“ኢትዮጵያ በእንግዳ ተቀባይነት ልዩ ስጦታዋ በቱሪዝምና በንግዱ ዘርፍ ባለሃብቶችን ለመቀበል ትልቅ አቅም አላት” በማለት ማስታወቃቸውን ኳታር ትሪቢዩን ዘግቧል።
ሰፊ በሆነ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ ያለችና የግብአት አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ጠቁመው፤ ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያለችበት ስራቴጂካዊ ቀጠናና በሁሉም አቅጣጫ ተደራሽ የሆነው አየር መንገዷ ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች የሁለትዮሽ ትስስር ተግባራት ተመራጭ እንደሚያደርጋት አስታውቀዋል።
አምባሳደሯ አክለውም ከኳታር ወደ አዲስ አበባ የ3 ሰዓት ተኩል ጉዞ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጎብኘትና የኢንቨስትመንት መስኮችን መፍጠር እንደሚቻልም አብራርተዋል።