የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ሳይንስ ተማሪዎች ምረቃ

ተማሪዎች ምረቃ

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ሳይንስ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት አምስት ዓመታት ያስተማራቸውን ከ700 በላይ ተማሪዎች በሁለተኛ ምእራፍ ለ16ኛ ጊዜ ነው ያስመረቀው።

ያለፈው 2013 ዓ.ም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሀገሪቷን የገጠመው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመማር ማስተማር ላይ ተግዳሮት ገጥሞት የነበረ ቢሆንም፤ ፈተናዎቹን በመቋቋም ተማሪዎችን እያስመረቀ  መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ባገኙት እውቀት ህዝብና ሀገራቸውን መጥቀም እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።

በሚልኪያስ አዱኛ