የዋጋ ጭማሪን ለመግታት የኀብረት ስራ ማኅበራት ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – በምርቶችና ሸቀጦች ላይ የሚታየውን አግባብ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለመግታት የኅብረት ስራ ማኅበራት ሚናቸዉ የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

”የኅብረት ስራ ግብይት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ 8ተኛ ሀገር አቀፍ የኀብረት ስራ ኤግዚብሽን ባዛርና ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የፌደራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዑስማን ሱሩር የኅብረት ስራ ማህበራት ያሉባቸዉን የአደረጃጀትና አሰራር ችግር፣ የፋይናንስ እጥረት፣ የሰለጠነ የሰዉ ሃይልና ኋላ ቀር የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን መቅረፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ማኅበራት በከተሞች አካባቢ በግብርና ምርቶችና ሸቀጦች ላይ የሚስተዋለዉን ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የማረጋጋት ስራ በማከናወን ሃላፊነታቸውን  እየተወጡ ነው ተብሏል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሳኒ ረዲ በበኩላቸው፣ ኅብረት ሥራ ማህበራት ብዙ ሆነን አንድ የምንሆንበት ወሳኝ ዘርፍ በመሆኑ ሚናቸውን ማጉላት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

(በሰለሞን በየነ)