ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በዓለም ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ29ኛ ጊዜ “ትምባሆን ያጨሳሉ? እንግዲያውስ ለማቆም ቆራጥ ይሁኑ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
ትምባሆ እንደልብ፣ ካንሠር፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ እና የስኳር ህመም ላሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነትን የሚጨምር እንዲሁም አጫሾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለጽኑ ህመምና ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አሳይቷል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው ባለማጨስ ጤናማ ይሁኑ! የሚያጨሱ ከሆነም ለማቆም የሚያስችል እርዳታን ያግኙ ብለዋል፡፡