ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – «ደም በመስጠት የዓለምን የልብ ምት እናስቀጥል» የሚል መርህ በኢትዮጵያ የዓለም የደም ለጋሾች ቀን ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለሁሉም የሃገሪቱ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ደም በመለገስ የወገኖቻችሁን ህይወት ለማሰቀጠል ለምታበረክቱት ውድ ስጦታ ከልብ አመሰግናለው ያሉት ሚኒስትሯ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት ደም መለገስን ባህል በማድረግ የበኩላቸውን አስትዋጽኦ እንዲያደርጉ እጠይቃለሁም ሲሉ ነው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው የገለጹት።
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን በየአመቱ በፈረንጆቹ ሰኔ 14 ቀን ይከበራል።