የአፍሪካ ህፃናት ቀንን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – “ልዩ ጥበቃ እና ሰላም ለኢትዮጵያ ህፃናት” በሚል መሪ ሀሳብ የአፍሪካ ህፃናት ቀንን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የውይይት መድረኩ በአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ነው፡፡

በውይይቱ የከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሜሮን አራጋውን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ  አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)