የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥላሁን ከበደን ርዕሰ መስተዳድር አድረጎ ሾመ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን

ነሐሴ 13/2015 (አዲስ ዋልታ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጥላሁን ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ።

ጥላሁን ከበደ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የስራ ኃላፊነት የህዝብ አገልጋይ ሆነው የሰሩና ብቃት ያለው አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ መሆናቸውም በምክር ቤቱ ተገልጿል።

ጥላሁን ከበደ ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣታቸውና የህዝብን ድምጽ የሚያከብሩ እንዲሁም በብዝሀነት የሚያምኑ አመራር እንደሆኑ በምክር ቤቱ አባላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳድሩን ሹመት በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጸሀይ ወራሳ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ ወላይቴ ቢቶ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡