የመጀመሪያው ዙር ግንባታው የተጠናቀቀው የደወሌ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆያ ተርሚናል የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።
በዘጠኝ ሄክታር መሬት ላይ ከጅቡቲ ተጎራባች በሆነው የሶማሌ ከልል ደወሌ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ተርሚናሉ የወጭ እና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያቀላጥፍ ተገልጿል።
የተርሚናሉ ሁለተኛ እና ሶስተኛው ምዕራፎች ሲጠናቀቁ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሠረተ ልማቶች ማዕከላት እንደሚኖሩት ታውቋል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት የሱማሌ ክልል ርዕሰ -መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ሌሎችም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የደወሌ እና ሲቲ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ዑጋዞች እና ሌሎችም ነዋሪዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።