የደገሀቡር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ተጣለ

ግንቦት 27/2013 (ዋልታ) – በ800 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ የደገሀቡር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ተጣለ።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ለውጡን ተከትሎ የክልሉን ህዝብ በየዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

የክልሉ ውሃ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አብራህማን አህመድ ሀሰን በበኩላቸው፣ ከተማዋ በቀን ከ9 ሺህ ሜትር ክዩብ በላይ ውሃ እንደሚያሥፈልጋት ገልጸው፣ ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ከስምንት ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

አክለውም ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑት የዞኑና አከባቢ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጫ ሥነሥርዓቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።