የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መልዕክት የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላለፉ

ጥቅምት 6/2014 (ዋልታ) የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ የሱፍ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ደመቀ በድጋሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያን ወደ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት እና ምጣኔሃብታዊ ብልጽግና ለመምራት የተሰጣቸውን እምነት ያሳያል ብለዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም በሁለቱ አገራት እና ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ እና የወንድማማችነት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።