ለደቡብ ዕዝ አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

ጥቅምት 6/2014 (ዋልታ) የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጠ።
የማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ የማዕረግ ዕድገት የሰራዊቱን ግዳጅ አፈፃፀም ወደተሻለ ደረጃ ከማሸጋገሩም በላይ የሰራዊቱን ተነሳሽነት ከፍ ያደርጋል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ይጠቁማል።
የማዕረግ ዕድገት ሲሰጥ ለተሻለ የሥራ ኃላፊነት እና ለውጤታማ ግዳጅ አፈፃፀም መሆኑን ተረድቶ በተመደቡበት የሥራ መስክ ላይ ውጤት ማምጣት እና ለሚመሩት ሰራዊት በሁሉም ዘርፍ አርኣያ መሆን ይጠበቃልም ነው ያሉት።