የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) ለ19 የካቢኔ አባላት ሹመት እንደሚሰጥ የሚጠበቀው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ መኩሪያ ጉርሙ ምክር ቤቱ የሕዝብ ውክልናን በመያዝ በ34 ጽሕፈት ቤቶችና በ10 ወረዳዎች ላይ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎችን ይተገብራል ብለዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የ2014 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ስራዎች እቅድ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱ ለ19 የካቢኔ አባላት ሹመት እንደሚሰጥም ተጠቁሟል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት