የጋምቤላ ክልል ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ

የካቲት 12/ 2013 (ዋልታ) – የጋምቤላ ክልል ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል 10 ሚሊዮን ብር ለመለገስ መወሱኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳደሩ እንደገለጹት፤ የድጋፍ ውሳኔው የተላለፈውየክልሉ ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በተጨማሪም የካቢኔው አባላት ከወር ደመወዛቸው 50 በመቶውን ለመለገስ መወሰናቸውን አስታወቀዋል።

እንዲሁም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን የጤና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ለማገዝ ሁለት አምቡላንሶችን ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውንም አስረድተዋል።

በቀጣይም በክልሉ ሶስት ዞኖችና ወረዳዎች ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳደሩ ጠቁመዋል።

የክልሉ ካቢኔ በቅርቡ ወደ ትግራይ በማቅናት ድጋፉን እንደሚያደርስ ጠቁመዋል።

በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎችም በትግራይ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደጉም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።