የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብ ፎረም ጎን ለጎን ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንዡን (ፒኤችዲ) ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያን የግርብና ሪፎርም፣ በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችንና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ልማትን ለማስፋፋት መንግሥት እያከናወነው ስላለው ተግባር አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ እያደረገችው ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን የሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።