የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን በዓለ ሲመት ለመታደም ነዋሪዎች ወደ መስቀል አቀኑ

መስከረም 24/2014 (ዋልታ) – የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር) በዓለ ሲመት ለመታደም በርካታ ነዋሪዎች ወደ መስቀል አደባባይ በማቅናት ላይ ይገኛሉ፡፡

በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ዐቢይ አሕመድን ዶ/ር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በመሾሙ፤ በዓለ ሲመቱ ላይ ለመታደም እና የመንግስት ምስረታውን ለመደገፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ መስቀል አደባባይ በመጓዝ ላይ ይገኛል።

በዓለ ሲመቱ ከሰዓት በኋላ በመስቀል አደባባይ የሚከናወን ሲሆን የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚከናወን እንደሚሆን የከተማ አስተዳደሩ ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡