የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ

ሐምሌ 4/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በጉለሌ እጽዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ተፈሪ ፍቅሬና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያዊያን በአረንጓዴ አሻራው የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባና ከችግኝ ተከላው ባሻገር ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እያደረገች ያለውን የለውጥ ጉዞ መደገፍ ይገባቸዋል ብለዋል።

የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ለታለመው ግብ መሳካት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW