የጤና ሚኒስቴርና የደምና ቲሹ ባንክ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

ኅዳር 7/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ለአገር ኅልውና በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሃግብር አከናወኑ።

አመራርና ሰራተኞች ለኅልውና ዘመቻው ወርሃዊ ደመወዛቸውን ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የደም ልገሳ ባደረጉበት ወቅት አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ በርካታ ሰዎች ደም ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

ደም መለገስ ካለው ጠቀሜታ አንፃር ዜጎች ደም እንዲለግሱም ጥሪ አቅርበዋል።

በሚኪያስ ምትኩ