የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ውይይት ተካሄደ

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከስፔን ኮኦፕሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርዮ ፋነጁልን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በስፔሽሊቲና ሰብስፔሻሊቲ ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት የልዩ ህክምና እና ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና ላይ በጋራ በመስራት ሊያጠናክሩ በሚችሉባቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የስፔን ኤምባሲ በጤናው ዘርፍ ለሚያደርገው ድጋፍ የጤና ሚኒስትሯ ምስጋና ማቅረባቸውንም ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።