የጥምቀት በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል

ጥር 11/2015 (ዋልታ) የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ እና በጎንደር በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ታቦታቱ በትላንትናው ዕለት ከየአድባራቱ በካህናቱ፣ በዲያቆናቱ እንዲሁም በምዕመኑ ዝማሬ ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀት መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የዓለም ቅርስ ሲሆን በበዓሉ ላይም በርካታ የውጭ አገራት ጎብኚዎች በየዓመቱ ይታደማሉ፡፡

ሱራፌል መንግስቴ (ከጃንሜዳ) እና ዙፋን አምባቸው (ከጎንደር)