የጥምቀት በዓል በተለያዩ የዓለም አገራት በተለያየ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ተከበረ

ጥር 11/2015 (ዋልታ) የጁሊያን የዘመን አቆጣጠርን የሚጠቀሙ የተለያዩ ሀገራት የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልን በተለያየ ሃይማኖታዊ ሥርዓት አክብረዋል፡፡

ጥምቀትን በዛሬው ዕለት በድምቀት ከሚያከብሩት አገራት ውስጥ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ባሉባቸው እንደ ሩሲያ፣ ሰርቢያ፣ ዩክሬይን፣ ህንድ፣ ጆርጂያ እና ግብጽ ሲጠቀሱ ሌሎች አገራት በዓሉን የሚያከብሩት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ጥር 6 ነው፡፡

ብዙዎቹ አገራት በዓሉን የሚያከብሩት ልክ እየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀው በወንዝ ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ በመጠመቅ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታል፡፡

በሰርቢያ ደግሞ የጥምቀት በዓል በተለየ መልኩ መስቀልን በቀዝቃዛው የዳንዩብ ወንዝ ውስጥ ዋኝቶ ቀድሞ የመያዝ ዉድድር በማካሄድ ይከበራል፡፡