የጥምቀት በዓል በአደባባይ በህብረት ደምቀን የምንታይበት በዓል ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥር 11/2015 (ዋልታ) የጥምቀት በዓል በአደባባይ በህብረት ደምቀን የምንታይበት በዓል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

በዩኔስኮ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በአምልኮና በዝማሬ ፍፁም ትህትናና አንድነታችን የሚታይበት ነው ብለዋል።

ክርስቶስ ፈጣሪ ሆኖ ሳለ ለሰው ልጆች ያለውን ትህትና ማሳየቱንም ነው ከንቲባዋ የተናገሩት።

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰራ ቆይቷል ያሉት ከንቲባዋ ይህንኑ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከመከፋፈል ርቀን እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይኖርብናል፤ የሃይማኖት መቻቻል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ነው ያሉት።

በአብሮነታችን የጋራ እሴቶቻችን ልናጠናክር ይገባል ያሉት ከንቲባዋ የፀጥታ አካላት በዓሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በሱራፌል መንግስቴ