የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተመረቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በአማራ ክልል በቡሬ ከተማ የተገነባውን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ዛሬ መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ባለስልጣናት ፋብሪካውን ተዟዙረው መጎብኘታቸውን ኢፕድ ገልጿል።