የፓሪስ ኦሊምፒክ ተወዳዳሪ አትሌቶችና አሰልጣኞች ለዝግጅት ወደ ሆቴል ሊገቡ ነው

የፓሪስ ኦሊምፒክ የቴክኒክና ሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ ቢልልኝ መቆያ

ሚያዚያ 3/2016 (አዲስ ዋልታ) የፓሪስ ኦሊምፒክ ተወዳዳሪ አትሌቶችና አሰልጣኞች ከሚያዝያ 15 ጀምሮ ለዝግጅት ወደ ሆቴል እንደሚገቡ ተነገረ፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶችና አሰልጣኞች ጋር በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ማድረጉም ተገልጿል፡፡

አትሌቶች ከልምምድ ስፍራና ከሆቴል አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የነበሩ ክፍተቶች ሊቀረፉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የፓሪስ ኦሊምፒክ የቴክኒክና ሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ ቢልልኝ መቆያ የተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች ፍላጎትን መሰረት አድርጎ ደረጃውን በጠበቀ ሆቴል ከሚያዝያ 15 ጀምሮ ዝግጅት እንደሚጀመር ተናግረዋል።

ከልምምድ ስፍራ ጋር በተያያዘ ለሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ምክረ ሀሳብ እንደሚቀርብም ነው የገለጹት።

በመጪው ክረምት በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች እንደምትሳተፍ ይጠበቃል።

በሀብታሙ ገደቤ