የ15ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል አካል የሆነው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ

የ15ኛው የብሔር ብረሰቦችና ህዝቦች በአል አካል የሆነው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነስርአት በአዲስ አበባ ከተማ አበባ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ፡፡

“እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 15ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልክት “ኑ ኢትዮጵያን በአንድ መድረክ እንያት” በሚል  ከህዳር 24 እስከ 27 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄደው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነ ስርአት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በመክፈቻ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የባህል አውደርዕይው የኢትዮጵያ ህዝቦችን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በአንድ መድረክ በማስተዋወቅ አንድነቱን የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳውን የህወሓት ፅንፈኛውን ቡድን የመከላከያ ሰራዊቱ ድል ባደረገበት ማግስት በአሉ በመከበሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

በአውደርዕዩ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የክልል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም  ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የባህል ሉኡካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል፡፡

በሕይወት አክሊሉ