ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 2‚581 ተማሪዎችን አስመረቀ

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ39 የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 581 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 905 የሆኑት የመደበኛ የትምህርት መስክ የተመረቁ ሲሆን፣ 581 ደግሞ በኤክስቴንሽን ተምረው የተመረቁ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው 32 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።

በዩኒቨርሲቲው ከተመረቁ 2 ሺህ 581 ተማሪዎች መካከል 1008 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።

(በሱራፌል መንግስቴ)