ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው

በ1999 ዓ.ም የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረው የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርኃግብሮች ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 127 ተማሪዎች ለ12ኛ ጊዜ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርስቲው በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ መርኃግብር ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች መካከልም 1ሺህ 461 ወንድ እንዲሁም 6 መቶ 66 ሴት ተመራቂዎች ናቸው፡፡

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ፋራህን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::

(በሄብሮን ዋልታው)