መስከረም 5/2014 (ዋልታ) የጤናውን ዘርፍ ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የዲጂታል ጤና ስርዓት ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ዘመኑን የዋጀ የጤና ስርአት ዝርጋታን ውጤታማ ለማድረግ የዲጂታል ጤና ስርአት ያለው አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ባሉ ሁሉም የጤና ተቋማት የመረጃ ፍሰትና አያያዝን የተሳለጠ ለማድረግ በተያዘው እቅድ መሰረት የተበታተነ የነበረውንየመረጃ አያያዝ ወጥ ለማድረግ ተሰርቷል ተብሏል።
ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ከ7 የአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ይሰራል ተብሏል።
የጤናውን ዘርፍ ወደ ዲጂታል ስርዓት በማሳደግ ውስጥ የመረጃ ምንተፋ ወይም የሳይበር ጥቃትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያሻል ያሉት የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ይግዛው (ዶ/ር) ይህንኑ ያሰበ ስርዓትን የማበልጸግ ሥራ ይሰራል ብለዋል።
በሄብሮን ዋልታው