ጂያን ኢንፋቲኖ በድጋሚ የፊፋ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ጂያን ኢንፋቲኖ

መጋቢት 7/2015 (ዋልታ) የ52 ዓመቱ ሰዊዘርላናደዊ ጂያን ኢንፋቲኖ ፊፋ በፕሬዝዳንትነት ለተጨማሪ አራት ዓመት እንዲመሩ ተመረጡ፡፡

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) 73ኛ መደበኛ ስብስባውን የማህበሩ አባል አገራት በተገኙበት በአፍሪካዊቷ አገር ሩዋንዳ ኪጋሊ እያደረገ ይገኛል።

ኢንፋቲኖ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ያለምንም ተቀናቃኝ ለሦሰተኛ ጊዜ ምርጫውን ማሸነፋቸው ተገልጿል፡፡

ጂያን ኢንፋቲኖ ፊፋን ከአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2023 አስከ 2027 ድረስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደሚመሩ በስብስባው ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

ኢንፋቲኖ 2016 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሴፍ ብላተር ተክተው ፊፋን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ይገኛሉ፡፡

በሚኪያስ ምትኩ