መጋቢት 27/2015 (ዋልታ) ገዳ ባንክ አርሶ አደሩ መሬቱን አስይዞ በዝቅተኛ ወለድ ብድር እንዲያገኝ እድል ማመቻቸቱን አስታወቀ፡፡
በይፋ ስራ ከጀመረ ሦስት ወር የሆነው ባንኩ በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት አዲስ ቅርጫፉን ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት ወልዴ ቡልቶ ገዳ ባንክ አርሶ አደሩ እና ሰፊውን ማህበረሰብ መሰረት አድርጎ የሚሰራ ባንክ መሆኑን ገልጸው ከ51 በላይ ቅሮጫፎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አመልክተዋል።
ባንኩ አርሶ አደሩን እና ሰፊውን የህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው ያሉት የባንኩ ፕሬዝዳንት በተለይ አርሶ አደሩ በፋይናንስ ላይ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ በተለያዩ ከተሞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
የአዲሱ ትውልድ ባንክ በሚል ባንኩ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንደሚሰጥም አስታውቀዋል።
በቡላ ነዲ