የካቲት 12/2014 (ዋልታ) በስድስተኛው የአፍሪካ ኅብረት እና አውሮፓ ኅብረት የጋራ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብራስል ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤልጂየም ቆይታቸው ከአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል፣ ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ድር ሌየን እና ሌሎችም የአውሮፓ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙርያ ምክክር ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ የአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋርም ከጉባኤው ጎን ለጎን ውጤታማ ምክክርን አድርገዋል፡፡