ጠ/ሚ ዐቢይ በግንባታ ላይ ያለውን የዓባይ ድልድይ ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ባደረጉት አጭር ቆይታ በዓባይ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘውን በገመድ የተወጠረ ድልድይ የግንባታ ሁኔታ ተመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ድልድዩ ለመድረስ የሚያስችለውንም መንገድ ግንባታ ጎብኝተዋል።

ድልድዩ 380 ሜትር ርዝማኔ እና 43 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን መንገዱ 4 ነጥብ 7 ኪ.ሜ. ርዝማኔ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

ግንባታዎቹ በመጪው ዓመት የሚጠናቀቁ ሲሆን የፕሮጀክቱ 62 በመቶ መጠናቀቁን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW