ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ

ጥር 12/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚከተሉትን ሹመቶች እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡

1. አለሙ ስሜ (ዶ/ር) – የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
2. ሀብታሙ ተገኝ – የማዕድን ሚኒስትር
3. ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) – የግብርና ሚኒስትር

በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦
1. ማሞ ምሕረቱ – የብሔራዊ ባንክ ገዢ
2. አለምፀሐይ ጳውሎስ – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር
5. መለሰ አለሙ – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ እንዲሆኑ ሹመት መሰጠቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡