ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አርሶአደሮችን አመሰገኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያንን ለመመገብ ቀን ከሌት የሚተጉ አርሶ አደሮችን አመስግነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በየማሳው ያለ መታከት በመትጋት ሊመግቡን ደፋ ቀና የሚሉ ጀግኖቻችን ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አያይዘውም እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ በግብርናው ዘርፍ እንዲሁም ለአረንጓዴ ዐሻራ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ለማሳካት በቁርጠኝነት መረባረብ ያስፈልገናልም ነው ያሉት።