ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከትግራይና ከአማራ ክልል የንግድ ማኅበረሰብ አባላት፣ ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ

ግንቦት 14/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ እና ከአማራ ክልል ከተውጣጡ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት፣ ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ፡፡

«ያደረግነው ስብሰባ፣ ልዩነቶችን ፈትቶ ለጋራ ዓላማ በመቆም የዝናብ ወቅት ከመጀመሩ በፊት በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ያለመ ነበር» ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው።

የፌደራል እና የክልል አመራሮችን እንዲሁም የሁለቱን አካባቢዎች ተወካዮች ጨምሮ፣ 15 ሰዎች የሚገኙበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራዎቹን የሚያሳልጥ ይሆናልም ብለዋል ።