ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋና  አቀረቡ

                                            ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 21/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋና  አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በኋላ ዛሬ ጠዋት ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቼ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ገና በጅምር ላይ ያለውን ዴሞክራሲያችንን ለማጠናከር በምርጫ ሂደቱ ውስጥ የታዩ ተግዳሮቶች እና ክፍተቶችን በመገምገም ምን እንደተማርንባቸው ተወያይተናል ሲሉም አክለዋል፡፡