ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ደቡብ አፍሪካውያንን ባጋጠማቸው የተፈጥሮ አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

ሚያዝያ 6/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደቡብ አፍሪካውያንን ባጋጠማቸው የተፈጥሮ አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

በደቡብ አፍሪካ በትላትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አደጋው በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና በአደጋው ለተጎዱ ደቡብ አፍሪካውያን ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ኢትዮጵያ በአጋርነት አብራቸው እንደምትቆም አረጋግጠዋል፡፡