ጠ/ሚ ዐቢይ እና ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ አዲሱን የጅቡቲ ኤምባሲ መርቀው ከፈቱ

የካቲት 12/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በአዲስ አበባ የተገነባውን አዲሱን በኢትዮጵያ የጅቡቲ ኤምባሲን መርቀው ከፍተዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ የተለያዩ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች መገኘታቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡