ጠ/ሚ ዐቢይ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

መጋቢት 6/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ዘመናት ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትንም አጠናክረን ለማስቀጠል ተስማምተናል ነው ያሉት፡፡