ጠ/ሚ ዐቢይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች በተለያዩ ሀገራት ስኮላርሺፕ እንደተመቻቸላቸው ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የካቲት 21/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች በተለያዩ ሀገራት ስኮላርሺፕ እንደተመቻቸላቸው አስታወቁ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጥተዋል።

በእውቅና መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላቀ ውጤት አስመዝግበው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀላቀላቸውን ያረጋገጡ ተማሪዎች አበረታትተዋል።

በዚህም ለእውቅና ሽልማት የበቁ 273 ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው የላቀ አድማጭ እና የተማሩትን በአግባቡ ያስቀመጡት በመሆናቸው በቀጣይ በመንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ በተለያዩ ሀገራት የትምህርት እድል እንደተመቻቸላቸውም አብስረዋል።

በደረሰ አማረ